የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በማማር ማስተማሩ ልቆ ለመውጣትና በአገር አቀፍ ደረጃ የሚጠበቅበትን አገራዊ ተልእኮ ለመወጣት ይችል ዘንድ ከፍተኛ መዋለ ነዋይ ከመንግስት በማስፈቀድ ወደ ተግባር በመግባት የግንባታ ስራዎች አከናዉኗል፡፡ ከዚህም ውስጥ የማምረቻ እና የማስተማሪያ አገልግሎት የሚውል ፋብሪካ ዋናው ሲሆን፤ ይህ በአገራችን ኢንዱስትሪ ሞዴል የሚይዛቸው የፈትል፣ የሽመና፣ የሹራብ፣ የማጠናቀቂያ/ፊኒሺንግ፣ አጠቃላይ ኢንተግሬትድ፣ እስቶር፣ መካኒካል ወርክ ሾፕ እና ገራጅ የያዘ ነው፡፡ ይህን የፋብሪካ ፕሮጀክት በተሟላ እና በታሰበው መልኩ ወደ ስራ ለማስገባት ይቻል ዘንድ የምርት አይነት፣ የሚመረጡ ማሽኖች፣ የማሽኖች አቀማመጥ፣ የሚመረተው መጠን፣ አስፈላጊ ግብአቶች እና ደጋፊ /ዩቲሊቲ/ ማሽኖች በማጥናትና ዝርዝር የግዥ እስፔሲፊኬሽን የማዘጋጀት ሥራ መጠናቀቁን ለቡድኑ ተገልጾላቸዋል፡፡
ከጉብኝቱ በኋላ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስቴር ፕ/ር ሂሩት ወ/ማሪያም ለዚህ ኢንዱስትሪ ሞዴል ማሽኖች እንዲሟሉለት እና የታሰበው ግብ እንዲሳካ መድረክ በማዘጋጀት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር እንደምታመቻችልን ቃል ገብተዋል፡፡ በመጨረሻም ልኡካን ቡድኑ በተቋሙ ፋሽን አዳራሽ ዙሪያ ችግኝ በመትከል አሻራቸውን አኑረዋል፡፡
